ቀልዱን ይተውን ኦቦ ዳውድ !

ኦቦ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ ሰጡት በተባለው መግለጫ ሁለት ገራሚ ነጥቦች አንስተዋል

፩ በስልጠና ላይ ያሉ የኦነግ ወታደሮችን አመራሩ እንዳይጎበኝ ተደርጓል። ኦቦ ዳውድ ፓለቲካ ውስጥ ቆዩ እንጂ ፓለቲካ አያውቁም እንዴ ? አያሰኝም ? በስልጠና ላይ ያሉ የቀድሞ የኦነግ ወታደሮች ከአሁን በኃላ የኦነግ አይደሉም የክልሉ ፓሊስ አልያም የፌዴራል ሰራዊት እንጂ። ጎብኚም አያስፈልጋቸውም ፣ ከኦነግ ጋር ያላቸው ግንኙነት መበጠስ አለበት ! ተጠሪነታቸው ለህዝብ እንጂ ለፓርቲዎች አይደለምና።

፪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የእኛ ጦር የሰፈረበት አካባቢ ያለ እኛ እውቅና ለምን ሰፈረ ? ሲሉም ጠይቀዋል ኦቦ ዳውድ። ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት ጦሩ ለምን ትጥቁን ይዞ ቆየ የሚለው ነው። መንግስት ጦሩን የፈቀደው ቦታ የማስፈር መብት አለው ለፓለቲካ ፓርቲዎችም የማማከር ግዴታ የለበትም !

ኦቦ ዳውድ በህዝብ እንግልትና መከራ መጫወትዎን ያቁሙ። ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ተስማምተው ነው ወደ ሀገር የገቡት እንደሌሎቹ ፓርቲዎች በህጋዊ መንገድ ብቻ ይንቀሳቀሱ ። መንግስት ኦነግን በልዩ ሁኔታ የሚያይበት ትዕግስት ማብቃት አለበት !

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.